በትምህርት ሚኒስቴር ፍኖተ ካርታ ላይ የተካሄደዉ የሶስት ቀን ዉይይት ዉጤታማ እንደነበር ትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በቲዉተር ገጻቸዉ ገለጹ፡፡
አርትስ 18/12/2010
ዶክተር ጥላዬ በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርትና ሥልጠና ዘርፉ የቀጣዩን 15 ዓመታት ፍኖተ-ካርታ ላይ በተደረገዉ ውይይት ፍኖተ ካርታዉን የሚያዳብሩ ሀሳቦች ተገኝተዉበታል ብለዋል፡፡
ምኒስትሩ አሁን ያለዉ ፍኖተ ካርታ በረቂቅ ደረጃ መሆኑን ማሳሰብ እወዳለሁ ብለዋል፡፡