loading
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በምርጫ ጣቢያ 05 የክልል ምክር ቤት የምርጫ ወረቀት በመቀያየሩ ምርጫው ከ 2 ሰዓት ተኩል በላይ ዘግይቷል፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14፣ 2013 በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በምርጫ ጣቢያ 05 የክልል ምክር ቤት የምርጫ ወረቀት በመቀያየሩ ምርጫው ከ 2 ሰዓት ተኩል በላይ ዘግይቷል፡፡
በክፍለ ከተማው ወረዳ 3 በምርጫ ክልል 23 የቦሌ ክፍለ ከተማ የምርጫ ወረቀቶች በስህተት በመላካቸው ነው ምርጫው በሰዓቱ ያልተጀመረው፡፡
በዚህ የምርጫ ክልል ለአዲስ አበባ ክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩት ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ሆነው የቀረቡት ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ በስፍራው ተገኝተው በጄኔራል ጃጋማ ኬሎ መታሰቢያ ጤና ጣቢያ ተገኝተው የችግኝ ተከላ ስነ ስርዓት አካሂደዋል፡፡

ወረቀቶቹ ተጓጉዘው ምርጫው እስኪጀመር መራጩ ህዝብ በትግዕስት እየተጠባበቀ መሆኑን በስፍራው የሚገኘው ባልደረባችን አክሊሉ ማሬ ዘግቧል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለመምረጥ በዚሁ የምርጫ ጣቢያ በተገኙበት ወቅት በችግኝ ተከላው መርሃ ግብር ተካፍለዋል፡፡
6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በመላ ሀገሪቱ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ሲሆን ህዝቡ ድምፁን በሚሰጥበት ወቅት የኮቪድ-19 የጥንቃቄ መንገዶችን እዲተገብር መልእክት ተላልፏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *