በአሜሪካ አንድ ሆስፒታል ውስጥ በተከሰተ የቫይረስ ወረርሽኝ ስድስት ልጆች ሞቱ
ቢቢሲ እንደዘገበዉ ዋናኩ በተባለው የእንክብካቤና የማገገሚያ ማዕከል ውስጥ በሚገኙ ህፃናት ታካሚዎች መካከል በአጠቃላይ 18ቱ በቫይረሱ መያዛቸውን የግዛቲቱባለስልጣናት እረጋገጠዋል።
አዴኖቫይረስ የሚባለው የወረርሽኙ መነሻ ቀላል ህመምን የሚያስከትል ቢሆንም፤ ነገር ግን የተያዙት ህፃናት ጤና በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ስለነበረ ውጤቱን የከፋ እንዳደረገውባለስልጣናቱ ተናግረዋል።
በግዛቲቱ በተከሰተው የቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ ምርመራ እየተካሄደ ሲሆን የህክምና ማዕከሉም አዲስ ህሙማንን መቀበል አቁሟል።
የምርመራ ቡድኑ በህክምና ማዕከሉ ውስጥ “ቀላል የእጅ መታጠቢያ ስፍራ ችግር” መመልከቱን ጠቁሟል። ነገር ግን የቫይረሱ ወረርሽኝ እንዴትና መቼ እንደተከሰተ በትክክልለማወቅ የሚያስችል መደምደሚያ ላይ አልተደረሰም።
የግዛቲቱ የጤና መስሪያ ቤትም ከጤና ማዕከሉ ጋር ወረርሽኙን መቆጣጠርን በተመለከተ በቅርበት መስራቱን እንደቀጠለም አሳውቋል።