loading
በአብዬ በሰላም ማስከበር ግዳጅ ላይ ለተሰማሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የመጀመሪያ ዙር የኮቪድ- 19 ክትባት ተሰጣቸው፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6 ፣ 2013  በአብዬ በሰላም ማስከበር ግዳጅ ላይ ለተሰማሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የመጀመሪያ ዙር የኮቪድ- 19 ክትባት ተሰጣቸው፡፡ በሱዳን አብዬ ግዛት የሚገኙት የ25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስለባሪ ሻለቃ አባላት አስትራዜኒካ የተባለው የመጀመሪያ ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ነው የተሰጣቸው፡፡ የሻለቃው የህክምና ሃላፊ ሻለቃ ፀሃይ በላቸው ሰራዊቱ እራሱን ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመከላከል የተሰጠውን አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ድርብ ሃላፊነት በብቃት ለመወጣት ሁሉም አባላት መከተባቸው የሚሰጣቸውን ግዳጅ ለመፈፀም የተሻለ ሁኔታን እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል፡፡

የሻለቃው ደረጃ አንድ ሆስፒታል የቴክኒክ ሃላፊ ሻለቃ ዶክተር ደረጄ ነጋሽ በበኩላቸው ሰራዊቱ ክትባቱን መውሰዱ እንዳለ ሆኖ ወረርሽኙን በሙሉ አቅም መከላከል እንዲቻል ከዚህ በፊት በዓለም የጤና ድርጅት የተቀመጡትን የኮቪድ 19 መከላከያ ዘዴዎች መተግበር ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግን ፣ ርቀትን መጠበቅ ፣ እጅን በሳሙና እና በውሃ ደጋግሞ መታጠብን እንዲሁም ሳኒታይዘር መጠቀምን ያለምንም መዘናጋት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

በሻለቃው የጤና ሙያተኞች የቅድመ ክትባት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በበቂ ሁኔታ መሰጠቱ አባላቱ በፍላጎት እንዲከተቡ እድል መፍጠሩ ከኢፌድሪ የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘና ያሳያል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *