loading
በአዲስ አበባ የጎዳና ተዳዳሪዎችን የማንሳት ስራ እንደቀጠለ ነው

በአዲስ አበባ የጎዳና ተዳዳሪዎችን የማንሳት ስራ እንደቀጠለ ነው

ከሶስት ቀናት በፊት የተጀመረው የጎዳና ተዳዳሪዎችን ከአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የማንሳት ከታቀደዉ በላይ ማንሳተ ተችሏል አለ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ፡፡

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ አለሙ አሰፋ ለአርትስ እንደተናገሩት ባለፉት ሁለት ቀናት ከአራት ክፍለ ከተሞች በፍቃደኝነት ከጎዳና አንስተን ወደ ተዘጋጀላቸው ማዕከላት ያስገባናቸው ከተጠበቀው ቁጥር በላይ መሆኑን ነግረውናል፡፡

በየቀኑ እስከ 1500 የጎዳና ተዳዳሪዎችን ለማንሳት የታቀደ ቢሆንም ቁጥሩ ከእጥፍ በላይ መሆኑንና፤ ከተጠበቀው በላይ መሆኑ መጠነኛ  ጫና መፍጥሩን ተናግረው ጥሩ ጎኑ እንደሚያመዝን ግንአልደበቁም፡፡

የጎዳና ተዳዳሪዎቹ በፍቃደኝነት ወደየማዕከላቱ ባይገቡ ኖሮ በግዳጅ የማስገባቱ ስራ ከባድ ሊሆን እንደሚችል በመገመት ፤ ቀጣይ ስራዎች እየቀለሉ ነው ብለውናል፡፡

በአዲስ አበባ 50 ሺ የሚጠጉ የጎዳና ተዳዳሪዎችን የማንሳቱ ስራ ሲጀመር፤ቀጣይ እጣፈንታቸው ላይ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒሲቴር ከክልሎች ጋር እንደተወያዩ ያስታወሱት አቶ አለሙ፤ ስልጠናዎች ከተሰጡ በኋላ ከክልል የመጡት እንደሚመለሱ ነግረውናል፡፡ በአዲስ አበባ የሚቀሩትንም ወደ ስራ ለማስገባት የከተማ አስተዳደሩ ሁለት መቶ ሚሊየን የሚጠጋ በጀት መመደቡን ነግረውናል፡፡

ማንኛዉም ዜጋ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ለመርዳት 6400 ላይ (A) ን በመላክ ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻል መገለጹ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *