loading
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቡና ከሀዋሳ የሚያርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቡና ከሀዋሳ የሚያርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

የሊጉ የ11ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራል፤ በሊጉ አናት ላይ የተቀመጠው ኢትዮጵያ ቡና 11፡00 ሲል ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከተገኘው ሀዋሳ ከነማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታል፡፡

ክልል ላይ ሀዋሳ ላይ ደቡብ ፖሊስ ከ ሲዳማ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታም በደቡብ ደርቢ ይጠበቃል፤ መቐለ ላይ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በትግራይ ስታዲየም ባህር ዳር ከነማን ያስተናግዳል፡፡

በድሬዳዋ ስታዲየም ድሬዳዋ ከነማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡ ክልል የሚደረጉ ሁሉም ጨዋታዎች በተመሳሳይ 9፡00 ይከናወናሉ፡፡

ነገ በዕለተ ከተራ ጎንደር ላይ ፋሲል ከነማ በፋሲለደስ ስታዲየም ወላይታ ድቻን ረፋድ 4፡00 ሲል ሲያስተናግድ እንዲሁም መከላከያ ስሑል ሽረን በ11፡00 ይገጥማል፡፡

ዕሁድ ደግሞ ደደቢት ከ አዳማ ከተማ በትግራይ ስታዲየም 9፡00 ሲል ይፋለማሉ፡፡

በሳምንቱ መርሀግብር ወጥቶለት የነበረው የመቐለ 70 እንደርታ እና ጅማ አባ ጅፋር ጨዋታ በኮንፌዴሬሽን ግጥሚያ ምክንያት ለየካቲት 21/2011 ተላልፏል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ሊጉን በ19 ነጥብ ሲመራ፤ ሀዋሳ በ17 ይከተላል፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ፋሲል ከነማና ባህር ዳር ከነማ በተመሳሳይ 15 ነጥቦች በግብ ክፍያ ተበላልጠው ከሶስት እስከ አምስት ያለውን ደረጃ ተቆናጥጠዋል፡፡

ስሑል ሽረ፣ ደቡብ ፖሊስ እና ደደቢት ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *