loading
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ተሸነፈ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ተሸነፈ

በ12ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክልል ስታዲየም ላይ ዛሬ ሶስት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡

ወደ ትግራይ ያቀናው የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ቡና በባለሜዳው መቐለ 70 እንደርታ የ1 ለ 0 ሽንፈት ገጥሞታል፡፡

ለመቐለው ቡድን የአሸናፊነት ጎሏን የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ አማኑኤል ገብረሚካኤል በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡ መቐለ ድሉን ተከትሎ ደረጃውን አሻሽሏል፡፡

ሀዋሳ ላይ መከላከያን ያስተናደው ሲዳማ ቡና በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ከመረብ ባገናኛቸው ሁለት ግቦች ታግዞ 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ለሲዳማ ጎሎቹን አዲስ ግደይ እና መሐመድ ናስር ከመረብ አገናኝተዋል፡፡

ሽረ ላይ በስሑል ሽረ እና ድሬዳዋ ከነማ መካከል የተካሄደው ግጥሚያ ያለግብ በአቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

በነገው ዕለት እንዲሁ ሶስት ጨዋታዎች ሲከናወኑ፤ በሳምንቱ ተጠባቂ ግጥሚያ በአማራ ክልል ደርቢ ባህር ዳር ከነማ ፋሲል ከነማን በግዙፉ የባህር ዳር ስታዲየም ያስተናግዳል፡፡

በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲዬም አዳማ ከነማ ከ  ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፤ ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከነማ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ከሚገኘው ደቡብ ፖሊስ ጋር በደቡብ ደርቢ ይገናኛሉ፡፡

ሀሙስ ወላይታ ድቻ ወደ ጅማ አቅንቶ ከጅማ አባ ጅፋር ጋር ጅማ ስታዲዬም ላይ ይጫወታሉ፡፡

ክልል ላይ የሚከናወኑት ሁሉም ግጥሚያዎች በተመሳሳይ 9፡00 የሚደረጉ ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ በውጤት ማጣት ቀውስ ውስጥ የሚገኘውን ደደቢት 11፡00 ሲል ያስተናዳል፡፡ የቡናን ሽንፈት ተከትሎ ጊዮርጊስ በዚህ ጨዋታ ድል የሚቀናው ከሆነ ያለውን የነጥብ ልዩነት የሚያጠብ ይሆናል፡፡

ሊጉን ኢትዮጵያ ቡና በ22 ነጥብ ይመረዋል፤ ሲዳማ ቡና 20 ይከተላል፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ በተመሳሳይ 18 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ሊጉን ኢትዮጵያ ቡና በ22 ነጥብ ይመረዋል፤ ሲዳማ ቡና 20 ይከተላል፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ በተመሳሳይ 18 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ሀዋሳ ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ በ17 ነጥቦች አምስተኛ እና ስድስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡ ጅማ አባ ጅፋር፣ ደቡብ ፖሊስ እና ደደቢት ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *