loading
በኢትዮጵያ 37 ሺህ በሚሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑ ተገለፀ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25፣ 2013 በኢትዮጵያ 37 ሺህ በሚሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑ ተገለፀ::
በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ 37 ሺህ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ይፋ አድርጓል፡፡ ተቋሙ ባወጣው መረጃ “ሳይበር ሆርስ ግሩፕ” የተሰኘ የመረጃ ሰርሳሪ ቡድን አዲስ የኮምፒውተር ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ኮምፒውተሮች ላይ ለመልቀቅ ዝግጅት ማድረጉ ተደርሶበታል፡፡

ይህ ቫይረስ “ብላክ ፒራሚድ ዋር” የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን 37 ሺህ በሚደርሱ የሀገራችን ኮምፒውተሮች ላይ ማነጣጠሩ ተገልጿል፡፡
ይህ ቡድን ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት ጋር ተያይዞ በተለያዩ የሀገራችን ድረ-ገጾች ላይ የመበርበር ሙከራ ሲያደርግ መቆየቱም ታውቋል፡፡

በመሆኑም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ሁሉም የሳይበር ምህዳሩ ተጠቃሚዎች ተገቢውን የሳይበር ደህንነት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቡን ከኢመደኤ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *