በኤሌክትሪክ ኃይል ታሪፍ ላይ ጭማሪ ሊደረግ ነው::
በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚዎች ላይ የታሪፍ ጭማሪ ለማድረግ አስፈላጊው ሂደት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ ማሻሻያው ዝቅተኛ የኃይል ተጠቃሚዎችን አያካትትም ተብሏል፡
ቢቢሲ የኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለስልጣን ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ጌታሁን ሞገስን አናግሮ እንደዘገበዉ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪው በተለያዩ ደረጃዎች አልፎ ተቀባይነት ሲያገኝ ተግባራዊ እንደሚሆን ተናግረዋል።
አቶ ጌታሁን የታሪፍ ጭማሪ ማድረግ ያስፈለገበትን ምክንያት ለመጨረሻ ጊዜ የታሪፍ ጭማሪ ተደርጎ የነበረው ከ12 ዓመታት በፊት እንደነበረ አስታውሰው ”በየዓመቱ ከ10-15 በመቶ ድረስ የዋጋ ግሽበት ነበር፤ የውጪ ምንዛሬ ዋጋ ላይም ከፍተኛ ለውጥ ስላአለ ነዉ ብለዋል።
“ከዚህ በተጨማሪ መስሪያ ቤቱ እስከ 60 በመቶ የሚሆኑ የካፒታል ዕቃዎችን ገዝቶ የሚያስገባው በውጪ ምንዛሬ በመሆኑና መስሪያ ቤቱ በስፋት የሚጠቀምባቸው ብረት እና የምህንድስና ዕቃዎች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ስላለ የዋጋ ማሻሻያ እንድናደርግ ግድ ብሎናል ብለዋል፡፡