loading
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ለንደን ደርቢ አርሰናል ከ ዌስት ሃም ይጫወታል

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ለንደን ደርቢ አርሰናል ከ ዌስት ሃም ይጫወታል

የ22ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ከኤፍ ኤ ካፕ እና ካራባዎ ዋንጫ መልስ ይደረጋሉ፤ በዚህም ዛሬ ቀን 9፡30 በኦሎምፒክ ስታዲየም ዌስት ሃም ዩናይትድ በለንደን ደርቢ አርሰናልን ያስተናግዳል፡፡
ምሽት 12፡00 ላይ የፕሪምየር ሊጉ አናት ላይ የተቀመጠው ሊቨርፑል ወደ አሜክስ አቅንቶ ከብራይተን ጋር ይጫወታል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት በርንሊ ከ ፉልሃም፣ ካርዲፍ ሲቲ ከ ሀደርስፊልድ ታውን፣ ክሪስታል ፓላስ ከ ዋትፎርድ እንዲሁም ሌስተር ሲቲ ከ ሳውዛምፕተን ይገናኛሉ፡፡
የማውሪዚዮ ሳሪው ቼልሲ ስታንፎርድ ብሪጅ ላይ ምሽት 2፡30 ከራፋኤል ቤኔቲዙ ኒውካስትል ዩናይትድ ጋር ይጫወታል፡፡
ዕሁድ ደግሞ አመሻሽ 11፡15 ላይ ኢቨርተን በጉዲሰን ፓርክ ከበርንማውዝ ሲጫወቱ በዊምብሌ ቶተንሃም ሆትስፐር ከ ማንችስተር ዩናይትድ የሚያረጉት የሳምንቱ ተጠባቂ ግጥሚያ ምሽት 1፡30 ይከናወናል፡፡
ሠኞ ምሽት 5፡00 ማንችስተር ሲቲ ኢቲሃድ ላይ ወልቭስን ያስተናግዳል፡፡
ሊጉን ሊቨርፑል በ54 ነጥብ ይመራል፤ ማ.ሲቲ ደግሞ በ50 ይከተላል፤ ቶተንሃም በ48 እንዲሁም ቼልሲ በ44 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *