loading
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ምሽት ቼልሲ ከቶተንሃም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ምሽት ቼልሲ ከቶተንሃም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

የሊጉ የ28ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ትናንት ምሽት ጀምሮ እየተካሄዱ ነው፡፡

በምሽቱ አራት ያህል ግጥሚዎች የተከናወኑ ሲሆን ወደ ዌልስ ምድር የተጓዘው ኤቨርተን በጊልፊ ሲጉርድሰን ሁለት እና ዶሚኒክ ካልቨርት ሌዊን ተጨማሪ ግብ 3 ለ 0 በመርታት ጣፋጭ ድል አስመዝግቧል፡፡

ሀደርስፊልድ ታውን ደግሞ ጆን ስሚዝ ላይ ወልቭስን አስተናግዶ ሳይጠበቅ አስጋራሚ የ1 ለ 0 ድል አስመዝግቧል፡፡ ስቲቭ ሙኒዬ መደበኛው የጨዋታው ክፍለ ጊዜ ተጠናቅቆ በተሰጠው ጭማሪ ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡

አሰልጣኝ ክሎውድ ፑኤልን ካሰናበተ በኋላ በጊዜያዊ አሰልጣኞች እየተመራ ሜዳው ኪንግ ፓወር ላይ ብራይተንን ያስተናገደው ሌስተር ሲቲ ወደ ድል የተመለሰበትን የ2 ለ 1 ውጤት አስመዝግቧል፡፡

ዴማራይ ግሬይ እና ጀሜ ቫርዲ ሲያስቆጥሩ፤ ፕሮፐር ለባህር ወፎቹ ግብ ቢያስቆጥርም ቡድኑን ከሽንፈት ግን ልትታደገው አልቻለችም፡፡

ሴንት ጀምስ ፓርክ ላይ በርንሊን የገጠመው ኒውካስል ዩናይትድ 2 ለ 0 አሸንፏል፤ ስቻር እና ሎንግ ስታፍ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡

የፕሪምየር ሊጉ 28ኛ ሳምንት መርሀግብር ዛሬ ምሽት በርካታ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

ምሽት 4፡45 ላይ ሁለት ጨዋታዎች ሲደረጉ አርሰናል ኤመሬትስ ላይ ቦርንመዝን ይገጥማል፡፡ መድፈኖቹ በአሌክስ ኢዎቢ እና ስቴፋን ሌችስታይነር የመሰለፍ ነገር እርግጠኞች አይደሉም፡፡ ሜይትላንድ ኒልስ እና ሎረን ኮሴልኒ ከቀላል ጉዳታቸው አገግመዋል ተብሏል፡፡

በክላውዲዮ  ራኒዬሪ የሚሰለጥነው ፉልሃም ወደ ደቡብ ጠረፉ ሳውዛምተን አቅንቶ ሴንት ሜሪ ላይ ይጫወታል፡፡

ምሽት 5፡00 ላይ ደግሞ የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ስታንፎርድ ብሪጅ ላይ በቼልሲ እና በቶተንሃም መካከል ይከናወናል፡፡ ሳሪ በምሽቱ ግጥሚያ ለኬፓ የመሰለፍ ዕድል ይሰጡት ይሆን የሚለው ነገር ይጠበቃል፡፡

በተመሳሳይ በሚደረጉ ሌሎች ፍልሚያዎች የሊጉ መሪ ሊቨርፑል በአንፊልድ ሮድ ዋትፎርድን ያስተናግዳል፡፡

ብራዚላዊው ሮቤርቶ ፊርሚኖ በምሽቱ ጨዋታ መሰለፍ ዕድል ቢኖረውም አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ከዚህኛው ጨዋታ ይልቅ ለመርሲ ሳይዱ የደርቢ ግጥሚያ ዝግጁ እንዲሆን ላያሰልፉት እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡

የላንክሻየሩ ማንችስተር ዩናይትድ ወደ ለንደን በመጓዝ ሴል ኸረስት ፓርክ ላይ ክሪስታል ፓላስን ይገጥማል፡፡

ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር የመጀመሪያ ቡድኑ ዘጠኝ ያህል ተጫዋቾችን ሳይዝ ወደ ሜዳ የሚገባ ሲሆን፤ አንደር ሄሬራ፣ አንቶኒ ማርሽያል፣ ጄሴ ሊንጋርድ፣ ዩሃን ማታ፣ ፊል ጆንስ እና ኒማኒያ ማቲች እንደማይሰለፉ ሲረጋገጥ፤ የማርከስ ራሽፈርድ  ገዳይ አጠራጣሪ ነው ተብሏል፡፡

ማቲዎ ዳርሚያን እና አንቶኒዮ ቫሌንሲያ አሁንም ወደ ሜዳ የማይመለሱ ሲሆን ተከላካዩ ማርኮስ ሮሆ ሊሰለፍ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

የፔፕ ጓርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ ኢቲሃድ ላይ ከዌስት ሃም ዩናይትድ ጋር ይጫወታል፡፡

ሲቲዎች ያለ ሁነኛ ተጫዋቾቻቸው ፈርናዲንሆ እና አይመሪክ ላፖርት የማይጫወቱ ሲሆን ጆን ስቶንስ እና ጋብሪዬል ጀሱስ አሁንም ጉዳት ላይ ናቸው፡፡

የቀድሞ ክለባቸውን የሚገጥሙት ማኑኤል ፔሌግሪኒ አዲስ የተጫዋች ጉዳት እንደሌለባቸው አስታውቀዋል፡፡ የደረጃ ሰንጠራዡን ሊቨርፑል በ66 ነጥብ ይመራል፤ ሲቲ በ65 ይከተላል፤ ቶተንሃም በ60 ሶስተኛ፣ አርሰናል በ53 4ኛ፣ ማንችስተር ዩናይትድ በ52 5ኛ እንዲሁም ቼልሲ በ50 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *