loading
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የበዓል ሰሞን ጨዋታዎች ትናንት መካሄድ ጀምረዋል፤ ዛሬም ይቀጥላሉ

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የበዓል ሰሞን ጨዋታዎች ትናንት መካሄድ ጀምረዋል፤ ዛሬም ይቀጥላሉ

በሊጉ የ21ኛ ሳምንት መርሃግብር (የበዓል ሰሞን ጨዋታዎች) ስድስት ያህል ፍልሚያዎች ዛሬ ይከናወናሉ፡፡

ምሽት 4፡45 በስታንፎርድ ብሪጅ ቼልሲ የሀሰንሁተሉን ሳውዛምፕተን ያስተናግዳል፤ ፔድሮ፣ ሲሴክ ፋብሪጋስ፣ ሮበን ሎፍተስ ቺክ፣ ካሉም ሁድሰን ኦዶይ እና ዳኒ ድሪንክ ዋተር በዚህ ጨዋታ ላይሰለፉ እንደሚችል ይጠበቃል ተብሏል፡፡

በርንማውዝ ከ ዋትፎርድ፣ ሀደርስፊልድ ከ በርንሊ፣ ዌስት ሃም ከ ብራይተን፣ ወልቭስ ከ ክሪስታል ፓላስ በተመሳሳይ ሰዓት 4፡45 ይጫወታሉ፡፡

ምሽት 5፡00 ላይ ደግሞ በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ኒውካስትል የሶልሻየሩን ማንችስተር ናይትድ ያስተናግዳል፡፡ ከአንድ ወር በላይ ጉዳት ላይ የነበረው አሌክሲስ ሳንቼዝ በዛሬው ጨዋታ ሊሰለፍ እንደሚችል ሶልሻዬር ፍንጭ ሰጥቷል፡፡ ኢሪክ ቤይሊ በቅጣት፣ ክሪስ ስሞሊንግ እና ማርኮስ ሮሆ በጉዳት ከጨዋታ ውጭ ናቸው፡፡

ነገ የመጨረሻው ተጠባቂ ጨዋታ ኢቲሃድ ላይ በማንችስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል መካከል ይከናወናል፡፡

ትናንት ምሽት ሌስተር ሲቲ ኢቨርተንን 1 ለ 0 አሸንፏል፤ ኢምሬትስ ላይ አርሰናል በክላውዲዮ ራኔሬ የሚመራውን ፉልሃም 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት መርታት ችሏል፡፡ ወደ ዌልስ ያቀናው ቶተንሃም ሆትሰፐር ከ ካርዲፍ ሲቲ ጋር ተጫውቶ 3 ለ 0 ረትቷል፡፡  ሃሪ ኬን፣ ኢሪክሰንና ሶን ሂንግ ሚን ለስፐርሶች ድል፤ የግቦቹ ባለቤቶች ናቸው፡፡ ማንችስተር ሲቲ እስኪጫወት ድረስ በ48 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ተቆናጥጧል፤ ሊጉን ሊቨርፑል በ54 ነጥቦች ይመራል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *