በኦሮሚያ ክልል በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ ከ15 ሺህ በላይ የቀበሌ ቤቶች በፍተሻ ተገኙ
በኦሮሚያ ክልል በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ ከ15 ሺህ በላይ የቀበሌ ቤቶች በፍተሻ ተገኙ
አርትስ 04/04/2011
የክልሉ ከተማ እና ቤቶች ልማት ቢሮ የቤቶች ልማት እና ማስተላለፍ ዳይሬክተር አቶ ባይሳ ሂርኮ በፍተሻ ከተገኙት 15 ሺህ 582 የቀበሌ ቤቶች ውስጥ 80 በመቶዎቹ መኖሪያ መሆናቸውን ገልጸው፥ ቀሪዎቹ የንግድ ቤቶች ናቸው ብለዋል፡፡
ቢሮው እነዚህ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት አቅም ለሌላቸው ዜጎች መተላለፋቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
በክልሉ የተለያዩ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለጹት፥ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የመስጠት ተግባሩ ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም አሁንም በሚገባ እንዳልተሰራበት ተናግረዋል፡፡
አቶ ባይሳ በቅርቡ እየተሰራ ባለው የመለየት ስራ የደረሳቸውን ጥቆማ ተከትሎ በተደረገ ማጣራት ሦስት እና አራት ፎቅ እያላቸው በመንግስት ቤት የሚኖሩ ግለሰቦች እንዳሉም ገልጸዋል፡፡
እስካሁን በተሰራው ስራ የምዕራብ አርሲ ትንንሽ ከተሞች፣ ቦረና ዞን እና ሆለታ ስራቸውን በአግባቡ እየሰሩ የሚገኙ ሲሆን፥ በሌሎች ከተሞች ጀምሩ ያለ ቢሆንም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቶ ባይሳ አብራርተዋል፡፡
ከሆለታ በስተቀር ችግሩ በስፋት የሚታይባቸው በኦሮሚያ ክልል የአዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞች ሰፊ ስራ እንደሚጠበቅባቸው ተነግሯል።