loading
በከፍተኛ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ ምርመራ ስር ያሉት ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው መዝገባቸው ወደ አቃቤ ሕግ መተላለፉን ፖሊስ አመለከተ፡፡

በከፍተኛ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ ምርመራ ስር ያሉት ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው መዝገባቸው ወደ አቃቤ ሕግ መተላለፉን ፖሊስ አመለከተ፡፡

ፖሊስ ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውን ጠርጥሬያቸዋለሁ ካላቸው 19 ጉዳዮች መካከል የሁለቱ መርከቦች ግዥና ጥገና እና የሁለት ሆቴሎችን ግዥ በተመለከተ ሲያካሂደው የቆየውን ምርመራ አጠናቅቆ ለአቃቤ ሕግ ማስረከቡን ተናግሯል፡፡

ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው የተጠረጠሩባቸው ሌሎቹን ጉዳዮች ለአቃቤ ሕግ ለክስ መመስረቻ በሚፈቀድለት ጊዜ አጠናቅቃለሁ ብሏል፡፡

የተጠርጣሪ ጠበቆች፣ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቅቄያለሁ ብሎ ለአቃቤ ሕግ ካሳለፈ በኋላ፣ ምርመራ አካሂዳለሁ ማለቱ ትክክል እና ህጋዊ አይደለም፣ የዋስ መብታቸውም ሊከበር ይገባል ብለው ተከራክረዋል፡፡

ጉዳዩን የሚመለከተው፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎት፣ የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ ተጠርጣሪው የተጠረጠሩበት ከፍተኛ የሙስና ወንጀል በመሆኑ የዋስ መብት ነፍጎ አቃቤ ሕግ ክሱን እንዲመሰርት የ10 ቀናት ጊዜ ፈቅዶ ለጥር 2/2011 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በሌሎችም ተጠርጣሪዎች ላይ ፖሊስ ያቀረበውን ተጨማሪ ጊዜና የጠበቆችን ክርክር ለመወሰን ለይደር ቀጥሯል፡፡ ዘገበው የፋና ነው፡፡

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *