loading
በኮትዲቯር ፕሬዚዳተታዊ ምርጫ ያሸነፉት አላሳኒ ኦታራ ለተቃዋሚዎች የውይይት ጥሪ አቀረቡ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 01፣ 2013 በኮትዲቯር ፕሬዚዳተታዊ ምርጫ ያሸነፉት አላሳኒ ኦታራ ለተቃዋሚዎች የውይይት ጥሪ አቀረቡ:: የሀገሪቱ ህገ መንግስታዊ ካውንስል በሰጠው ማረጋገጫ ኦታራ ለሶስተኛ ጊዜ አገሪቱን መምራት የሚያስችል ድምፅ አግኝተዋል፡፡ የ78 ዓመቱ ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ በምርጫው 94 በመቶ የሚሆነውን የመራጮች ድምፅ አግኝተዋል ቢባልም ተቃዋሚዎች ውጤቱን አልተቀበሉትም፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ምርጫው ከጅምሩ ህገ መንግስታዊ ስላልሆነ አጥብቀው እንዲቃወሙ ለደጋፊዎቻቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ኦታራ ግን ህዝቡን ለብጥብጥ ከማነሳሳት ይልቅ ተቀራርቦ መወያየቱ መፍትሄ ያመጣልና በሰላማዊ መንገድ እንነጋገር እያሉ ነው፡፡ ኦታራ ገና ለሶስተኛ ጊዜ እንደሚወዳደሩ ይፋ ሲያደርጉ በተቀሰቀሰ ግጭት ከ50 ያላነሱ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፡፡ የቀድሞው የኮትዲቯር ጠቅላይ ሚኒስትርና የአሁኑ የተቃዋሚ መሪ ፓስካል አፊ ንግዌሳን የሽግግርምክር ቤት ለማቋቋም ተንቀሳቀወሰዋል በሚል ለእስር ተዳርገዋል ነው የተባለው፡፡ ሌሎች በተመሳሳይ ተግባር የተጠረጠሩ ግለሰቦችም ጉዳያቸው እየተጣራ እንደሆነ ዘገባው አክሎ ገልጸዋል፡፡ አሁንም ምርጫውን ተከትሎ የእርስበርስ ግጭት በመነሳቱ ሶስት ሰዎች መሞታቸውና 41
መቁሰላቸውን የአካባቢው ባለ ስልጣናት ተናግረዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *