loading
በዩጋንዳ የሞተር ሳይክል አምቡላንሶች የብዙዎችን ህይዎት እየታደጉ ነው፡፡

በዩጋንዳ የሞተር ሳይክል አምቡላንሶች የብዙዎችን ህይዎት እየታደጉ ነው፡፡

በርካታ  ዩጋንዳዊያን በመንገድ ችግር ሳቢያ የአምቡላንስ አገልግሎት ስለማያገኙ የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል፡፡

ይህን የተረዳው በሀገሪቱ የሚንቀሳቀስ አንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በብስክሌቶች እና በሞተር ሳይክሎች የሚጎተቱ አምቡላንሶችን በማዘጋጀት አገልግሎት መስጠት ጀምራል፡፡

በዚህ አገልግሎቱም በተለይ ነፍሰ ጡር ሴቶች የቅድመ ወሊድ ክትትል ለማድረግ  እንዲሁም ከወሊድ በኋላ የጤናቸውን ሁኔታ እንዲከታተሉ በእጅጉ አግዟቸወዋል ነው የተባለው፡፡

ሳንድራ ናይጋጋ የባለች ነፍሰ ጡር እነዚህን አምቡላንሶች ባታገኝ ኖሮ አደገኛ የጤና ችግር ላይ ልትወድቅ ትችል እንደነበር ገልፃ ይህ ግብረ ሰናይ ተቋም ላደረገላቸው ሁሉ ምስጋናዋን አቅርባለች፡፡

አብዛኞቹ የዩጋንዳ አካባቢዎች ከዋና ዋና መንገዶች ጋር በመንገድ ስላልተገናኙ በትራንስፖርት ችግር በቀላሉ ታክመው የሚድኑ ሰዎች ህይዎታቸው እንደሚያልፍ ይነገራል፡፡

አልጀዚራ በዘገባው እንዳስነበበው በዩጋንዳ በየቀኑ ከ15 የማያንሱ ሴቶች ከወሊድ ጋር በተያየዘ ችግር ለሞት ይዳረጋሉ፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *