loading
በዲሞክራቲክ ኮንጎ ባለፉት ሰድስት ወራት ብቻ ከ1 ሺህ 300 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ30፣ 2012  በዲሞክራቲክ ኮንጎ ባለፉት ሰድስት ወራት ብቻ ከ1 ሺህ 300 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል ተባለ:: የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ ባወጣው ሪፖርት እንዳለው 165 ህፃናትን ጨምሮ 1 ሺህ 315 ሰዎች ነፍጥ አንግበው በሚንቀሳቀሱ ሸማቂዎች ተገድለዋል፡፡በሀገሪቱ በተለይ በምስራቃዊ ኮንጎ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እየተባባሰ መምጣቱን ድርጅቱ ገልጿል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው በዲሞክራቲክ ሪብሊክ ኮንጎ አለመረጋጋት እና የሚደርሰው የመብት ጥሰት ከአምናው በሶስት እጥፍ ጨምሯል፡፡ በተለይ ኢቱሪ በምትባለው የሀገሪቱ ግዛት በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት በሰው ልጆች ላይ የሚፈፀሙ አሰከፊ ወንጀሎች ብሎ ዓለም አቀፉ የመንጀለኞች ፍርድ ቤት ከደነገጋቸው ወነጀሎች ጋር እንደሚስተካሉ ነው ቢሮው ያስታወቀው፡፡

ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ መንግስት በመላ ሀገሪቱ በሚንቀሳቀሱ ተዋጊዎች ላይ ይፋዊ ዘመቻ ቢያውጅም ችግሩን ማስወገድ አልቻለም፡፡ ዲሞክራቲክ ኮንጎ የኢቦላና የኮቪድ19 ስርጭትን ለመከላከል የውስጥ አለመረጋጋቷ ከባድ እቅፋት እንደፈጠረባት ይነገራል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *