loading
በግድቡ ዙያሪያ የማይናወጠው የኢትዮጵያ አቋም፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 12 ፣ 2013 ግብፅና ሱዳን የአፍሪካ ህብረትን የአደራዳሪነት ሚና ተቀብለው ወደ ሶስትዮሽ ድርድሩ እንዲመለሱ ኢትዮጵያ ጥሪ አቀረበች፡፡ ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ለፀጥታው ምክር ቤት በፃችፈው ደብዳቤ በአፍሪካ ህብረት የሚመራው ሂደት የፀጥታው ምክር ቤትን መርሆዎች መሠረት ያደረገና ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን የሚያፈላልግ መሆኑን ገልፃለች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቀቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ሁለቱ ሀገራት ድርድሩን በማኮላሸትና ሂደቱ ዓለም አቀፋዊ ይዘት እንዲላበስ በማድረግ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር የሚሄዱበት መንገድ ትክክል አለመሆኑን አመልክተዋል፡፡አቶ ደመቀ አክለውም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የሶስትዮሽ ድርድር የማይናወጥ አቋም እንዳላት በመግለፅ ይህን ሀሳብ ደግፈው ሶስቱን ሀገራት ለማቀራረብ ጥረት ያደረጉትን ደቡብ አፍሪካና
ሪፓብሊክ ኮንጎን አመስግነዋል፡፡

ይህም የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካዊያን መፈታት አለባቸው የሚለውን መርህ የሚያጠናክር በመሆኑ በሁሉም ዘንድ ሊከበር ይገባል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለምክር ቤቱ በጻፈችው ደብዳቤ ሁለተኛው የውሃ ሙሌት ከመጀመሩ አስቀድሞ የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ የነበራት ተነሳሽነት በግብፅና ሱዳን ዋጋ አለማግኘቱ ተመልክቷል፡፡ ግብፅና ሱዳን በግድቡ የውሃ አጠቃቀም ላይ የያዙት አስገዳጅ የሆነ ኢፍትሃዊ አቋም በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነት እንደሌለውና ሁሉንም ወደሚያግባባው የጋራ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረው ድርድር እንዲመለሱ ጥሪ ቀርቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *