በጠረፋማ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የእለት ፍጆታ እቃዎች እና አልባሳት ከቀረጥ ነጻ የሚገቡበት የፍራንኮ ቫሉታ አገልግሎት እንዲቋረጥ ተደረገ።
በጠረፋማ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የእለት ፍጆታ እቃዎች እና አልባሳት ከቀረጥ ነጻ የሚገቡበት የፍራንኮ ቫሉታ አገልግሎት እንዲቋረጥ ተደረገ።
አርትስ 03/04/11
አገልግሎቱ እንዲቋረጥ ያዘዘው ገቢዎች ሚኒስቴር ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ለታለመለት አላማ አልዋለም በሚል ነው።
ከመሃል ሀገር የሚርቁና መሰረተ ልማት የማይዳረስባቸው ጠረፋማ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የፍጆታ እቃዎች በድንበር የጉሙሩክ ስርአትን ተከትለው ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡላቸው ይደረግ ነበር።
ይሁን እንጂ ምርቶች ከታለመላቸው አላማ ውጪ መዳረሻቸው መሃል ሀገር በመደረጉ አገልግሎቱ የኮንትሮባንድ ምንጭ እየሆነ መጥቷል ብሏል ሚኒስቴሩ ።
ሚኒስቴሩ ባሳለፍነው ሳምንት በሰጠው መረጃ ኢትዮጵያ ከፈረንጆቹ 2015 እስከ 2018 አጋማሽ ድረስ በፍራንኮ ቫሉታ ምክንያት ብቻ ከ14 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ አጥታለች ይላል የኢዜአ ዘገባ።