loading
በጣሊያን ኮፓ አጣሊያ ኤስ ሚላን ከናፖሊ ተጠባቂ ጨዋታቸውን ዛሬ ምሽት ያደርጋሉ

በጣሊያን ኮፓ አጣሊያ ኤስ ሚላን ከናፖሊ ተጠባቂ ጨዋታቸውን ዛሬ ምሽት ያደርጋሉ

ይህ የኮፓ ኢጣሊያ የሩብ ፍፃሜ የምሽት ተጠባቂ ግጥሚያ በጁሴፔ ሜዛ የሚከናወን ሲሆን ምሽት 4፡45 ሲል ይጀመራል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ከሶስት ቀናት በፊት በዚሁ ሜዳ በሴሪ ኤው ተገናኝተው ያለግብ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

ሮዘነሪዎቹ የሚያሳዩትን ወጣ ገባ አቋም፤ ደጋፊው በሚፈልገው መንገድ ማስተካከል የተሳናቸው ሲሆን የዋንጫ ጥማቸውን ለመቁረጥ የዛሬው ጨዋታ ወሳኝ ነው፡፡

ከኤስ ሚላን ጋር የኮፓ ኢጣሊያን ዋንጫ ማሳካት የቻሉት የናፖሊው አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲ ግን ለጅናሮ ጋቱሶ ቡድን በቀላሉ እጅ ይሰጣሉ ብሎ መጠበቅ ያስቸግራል፡፡

አዲሱ የሚላን ፈራሚ ክሪስቶቭ ፒያቴክ የመጀመሪያ ሙሉ ጨዋታውን ያከናውናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ተጫዋቹ በሚላን ማሊያ የመጀመሪያ ጨዋታውን በሴሪ ኤው ግጥሚያ ተቀይሮ መግባቱ ይታወሳል፡፡

ክሪስቲያን ዛፓታ፣ ማቲያ ካልዳራ፣ ሉካስ ቢግሊያ እና ፔፔ ሬና ደግሞ በጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጭ ናቸው፡፡

ከቭላድ ችሪቼስ ውጭ የተጫዋች ጉዳት የሌለባቸው ናፖሊዎች፤ የቡድኑ የመጀመሪያ ተሰላፊ ተጫዋቾች በካርሌቶ በኩል  ዕረፍት ሊሰጣቸው እንደሚችል ተነግሯል፡፡

በሌሎች የሩብ ፍፃሜ ፍልያዎች ነገ ፊዮረንቲና ከ ሮማ እንዲሁም አታላንታ ከ ዩቬንቱስ ይገናኛሉ፡፡ ኢንተር ሚላን ደግሞ ሀሙስ ሳንሲሮ ላይ ላትሲዮን ያስተናግዳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *