loading
በፓሪስ የኮሮናቫይረስ ስርጭት በድጋሚ ማገርሸቱ ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2013 በፓሪስ የኮሮናቫይረስ ስርጭት በድጋሚ ማገርሸቱ ተሰማ::በፈረንሳይ ዋና ከተማና ፓሪስና ማርሴል የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በድጋሚ በማገርሸቱ ምክንያት በርካታ ተቋማት ለአገልግሎት ዝግ ሆነው እንዲቆዩ መወሰኑ ተሰምቷል፡፡

በሀገሪቱ ባገረሸው የኮቪድ 19 ስርጭት ምክንያት በዋና ከተማዋ ፓሪስ የሚገኙ የምሽት መዝናኛዎችና ሬስቶራንቶች ከማክሰኞ ጀምሮ ዝግ ሆነው እንዲቆዩ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ማዘዛቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ትላንት በወጣው የሀገሪቱ ሪፖርት መሰረት 12 ሺ 565 የኮቪድ 19 ኬዝ በመመዝገቡ በዋና ከተማዋ የሚገኙ የህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ዝግ ሆነው እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን፤ የደቡባዊቷ ከተማ ማርሴል ከሁለት ሳምንት በፊት የምሽት ቤቶች እና ሬስቶራንቶቿን ዘግታለች ፡፡

በከተማዎቹ የሚገኙ የምሽት ቤቶች እና የመጠጥ መሸጫ ሱቆች የተጠቃሚ ቁጥራቸውን በግማሽ ቀንሰው ፤ የንፅህና መጠበቂያዎችን በተገቢው መንገድ ለሟሟላት ጥረት ቢያደርጉም ፤ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ግን መጠጥና ምግብ ለሚፈልጉ ሰዎች ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ በየቤታቸው የማቅረብ ስራ እንዲሰሩ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡ባለስልጣናቱ አክለውም ለኛ ለፈረንሳውያን መዝናኛዎችን እና ሬስቶራንቶችን መዝጋት ከባድ ቢሆንም በሽታው የሚያደርሰውን ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት መጠንቀቁ ይበጃል በማለት ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በመልዕክታቸው አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

በማርሲል ከተማ ሁሉም የምሽት ቤቶች ሪስቶራንቶች የስፖርት ማዘውተሪያዎችን ጨምሮ የህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ፤ ቲያትር ቤቶች ፤ሙዚየሞች እና ፊልም ቤቶች የስርጭቱ መጠን ዝቅተኛ እስኪሆን ድረስ ዝግ ሆነው እንዲቆዩ መወሰኑ ተሰምቷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *