loading
ቤናሚን ኔታኒያሁ በፓርቲያቸው ውስጥ አዲስ የስልጣን ተቀናቃኝ ግለሰብ ተነስቶባቸዋል::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 ቤናሚን ኔታኒያሁ በፓርቲያቸው ውስጥ አዲስ የስልጣን ተቀናቃኝ ግለሰብ ተነስቶባቸዋል:: በጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያ የሚመራው የሊኩድ ፓርቲ ሁነኛ ሰው የሆኑት ጌዲዮን ሳር ራሳቸውን ከፓርቲው ማግለላቸውን አስታውቀዋል፡፡ ለዚህ ምክንያታቸው ደግሞ ኔታኒያሁ ከሀገራቸው ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም ያስቀድማሉ ስለዚህ ከሳቸው ጋር መስራት አልፈልግም የሚል ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት የምርጫ ተቀናቃኛቸው የነበሩትና አብረዋቸው የጥምር መንግስት የመሰረቱት ቤኒ ጋንትዝ የእስራኤል ምክር ቤት ፈርሶ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ የሚል የድጋፍ ድምፅ ሰጥተዋል፡፡ ሳር በመግለጫቸው ከኔታኒያሁ ጋር ከመስራት ይልቅ የራሳቸውን የፖለቲካ ፓርቲ መስርተው በቀጣይ ጊዜ በምርጫ ለመወዳደር እቅድ እንዳላቸው ይፋ አድርገዋል፡፡ ኔታኒያሁ የራሳቸው ምቾት እንዳይጓደል ነው ስልጣናቸውን የሚጠቀሙበት የሚሉት ሳር
ለዚህ መፍትሄው በእስራኤል አዲስ የአስተዳደር ዘይቤ ማምጣት ነው ብለዋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው የቀድሞው የጠቅላይ ሚንስትሩ ረዳትና የካቢኔ ሚኒስትር የነበሩት ጌዲዮን ሳር በሊኩድ ፓርቲ የወደፊቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዉ እንደሚሆኑ ይነገርላቸው ነበር፡፡በመሆኑም በመነቃነቅ ላይ ላለው የኔታኒያሁ መንበር የራሳቸው በዚህ መልኩ መነሳት ጫናው ቀላል እንደማይሆን ይታመናል፡፡ ኔታኒያሁ ፓርላማው እንዳይበተን ከተለያዩ ፓርቲዎች ጋር ድርድር እያደረጉ ቢሆንም ብዙ ድጋፍ ያገኙ አይመስልም፤ በመሆኑም ሀገሪቱ በሁለት ዓመት ወስጥ አራተኛ ምርጫ ማካሄዷ አይቀሬ ይሆናል እየተባለ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *