ብ/ጀነራል አሳምነው ፅጌ እና ብ/ጀነራል ተፈራ ማሞ በላሊላ አሸንድዬ ካባ ተደረበላቸው።
አሸንድዬ፣አሸንዳ ፣ሶለል እና ሻደይ የዓለም ሀብት የሚሆኑት በባለቤትነት ስንጠብቃቸው ነው ብለዋል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ፎዚያ አሚን። የአሸንድዬ የሴቶች በዓል “አሸንድዬ ለሰላምና አንድነት በፍቅር ለመደመር” በሚል መሪ ቃል በላሊበላ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው። በበዓሉ ላይ ብ/ጀነራል አሳምነው ፅጌ ወጣቶች ለሰላም ስሩ ሲሉ ብ/ጀነራል ተፈራ ማሞ ደግሞ ባህል የሚታወቀው አገር ሲኖር ነው ብለዋል ። አርትስ ቲቪ በላሊበላ ተገኝቶ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በዚህ መደሰታቸውን ተናግረዋል። በዓሉ በላሊበላ ቀጥሏል።