ቦኮሃራም በናይጄሪያ 19 ሰዎችን ገደለ።
ፕሬስ ቴሌቭዥን እንደዘገው ታጣቂው ቡድን ቦኮሃራም በሰሜን ምዕራብ የሃገሪቱ ክፍል በምትገኘው ማይላሪ ዘልቆ በመግባት በተሽከርካሪ የታገዘ የሮኬት ጥቃት ፈፅሟል።
ማንነታቸው ያልተገለፀ የእርዳታ ሰጭ ድርጅት ሰራተኞች የሟቾችን ቁጥር 63 አድርሰውታል።
የአካባቢው ነዋሪዎች ፖሊስ ጥቃቱ ሲፈጸም ህዝቡን ለመከላከል ምንም ዓይነት ሙከራ ባለማድረጉ ማዘናቸውን ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡
ቦኮሃራም ከፈረንጆቹ 2009 ጀምሮ እስካሁን ከ20 ሺህ በላይ ናይጄሪያውያንን ሲገድል፥ 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎችን ደግሞ አፈናቅሏል።