ትራምፕ ሜክሲኮ ከጓቲማላ እየገቡ ያሉ ስደተኞችን እንድታስቆም አስጠነቀቁ
አርትስ 12/02/2011
ሜክሲኮ ከጓቲማላ እየፈለሱ ያሉ ሰዎችን ካላስቆመች ከሜክሲኮ ጋር ባላት ድንበር ላይ ጦር እንደሚያቆሙ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስጠንቅቀዋል።
ባለፈው ሣምንት ከሆንዱራስ የተነሡ ሦስት ሺህ የሚሆኑ ስደተኞች ጓቲማላንና ሜክሲኮን አቋርጠው ወደ አሜሪካ መግባታቸውን ገልፀው ከእነዚህ ስደተኞች መካከል ወንጀለኞች መኖራቸውን እና ሜክሲኮ ይህን የማታስቆም ከሆነ አሜሪካ በሃገራቱ ድንበር ላይ ጠባቂዎችን እንደምታቆም ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዩናይትድ ስቴትስ በደቡብ ድንበሯ ላይ የሚጣሉ ጥቃቶች ከካናዳና ከሜክሲኮ ጋር የገባችባቸውን የንግድ ውሎችንም ይጎዳሉ ነው ያሉት፡፡
እንደ ሲ ጂ ቲ ኤን ዘገባ የትራምፕን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ከጓቲማላ በሜክሲኮ ድንበር የሚገቡ ስደተኞች በመጠለያ ፍለጋ እየተንከራተቱ ነው ተብሏል