loading
ትራምፕ ጀፍ ሴሽንስን ካባረሩ በኋላ መልካም ተመኝተውላቸዋል

ትራምፕ ጀፍ ሴሽንስን ካባረሩ በኋላ መልካም ተመኝተውላቸዋል

አርትስ 29/02/2011

 በነጩ ቤተ መንግስት ሰወች መባረራቸው ቀጥሏል፤ የአሁኑ ተረኛ  ደግሞ የአሜሪካው ጠቅላይ ኣቤ ህግ ጀፍ ሴሺንስ ሆነዋል፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው ሰሺንስ ተባረሩ የተባለው በ2016ቱ የአሜሪካ ምርጫ ከሩሲያ ጣልቃ ገብነት ጋር ከሚደረገው ምርመራ ጋር በተገናኘ ነው፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራፕ ጠቅላይ አቃቤ ህጉን  ለጊዜው የጽህፈት ቤት ሀላፊያቸው ማቲው ዊታከር ይተኳቸዋል ካሉ በኋላ ሴሺንስ ለሰጠን አገልግሎት ግን መልካሙን ሁሉ እንመኝለታለን ብለዋል፡፡

የቀድሞው የአላባማ ሴናተር እና የትራምፕ ቀንደኛ ደጋፊ የነበሩት ተሰናባቹ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የመልቀቂያ ደብዳቤያቸው በራሳቸው ፈቃድ የተፈፀመ እንዳልሆነ ገልፀዋል፡፡

የተከበሩ ፕሬዝዳንት ሆይ እነሆ ባዘዙኝ መሰረት የመለልቀቂያ ጥያቄዬን አቅርቤያለሁ የሚል ቀን ያልተፃፈበት ደብዳቤ መፃፈቸውንም የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *