loading
ቻይና እኛም ቤት ሚሳኤል አለ የሚል መልእክት ለአሜሪካ አስተላልፋለች

 

ቻይና እኛም ቤት ሚሳኤል አለ የሚል መልእክት ለአሜሪካ አስተላልፋለች

አሜሪካ የቅኝት ነፃነት በሚል ሰበብ በደቡባዊ ቻይና ባህር የምታደርገው የቅኝት እንቅስቃሴ ያሰጋት ቤጂንግ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን ለማሰማራት መወሰኗን ይፋ  አድርጋለች፡፡

ሲ ኤን ኤን እንደዘገበው ቻይና አሰማራቸዋለሁ ያለቻቸው ዲ ኤፍ 26 የተባሉት ሚሳኤሎች እስከ 5 ሺህ 471 ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጠው ተፈላጊው ኢላማ መምታት የሚችሉ ናቸው፡፡

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሉ ካንግ አሜሪካ በተደጋጋሚ ሉዓላዊነታችንን ከሚፈታተን ድርጊት እንድትታቀብ ስንነግራት ካልሰማች አስፈላጊውን እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል፡፡

ቤጂንግ  አሜሪካ በደቡባዊ ቻይና ባህር አካባቢ የምታደርገው እንቅስቃሴ የሀገራችንንም ዓለም አቀፉንም ህግ የሚጥስ ነው ስትል አሜሪካን ትከስሳለች፡፡

ከዋሽንግተን በኩል የሚሰጠው መልስ ግን ሁሌም በነፃነት የመንቀሳቀስ መብቴን የሚጋፋኝ አካል ሊኖር አይችልም የሚል ነው፡፡

ቻይና የቱንም ያህል ማስጠንቀቂያ ብትሰጥም እስካሁን ከአሜሪካ በኩል የተለወጠ ነገር ባለመኖሩ የፕሬዝዳንት ሽ ዢንፒንግ አስተዳደር እኛም እራሳችንን እንዴት መከላከል እንደምንችል ይወቁ በሚል ነው እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *