ቼልሲ በሁለት የዝውውር መስኮቶች ላይ እንዳይሳተፍ በፊፋ እገዳ ተጣለበት
ቼልሲ በሁለት የዝውውር መስኮቶች ላይ እንዳይሳተፍ በፊፋ እገዳ ተጣለበት
የዓለም እግር ኳስ አስተዳዳሪው አካል (ፊፋ) የስነ ምግባር ኮሚቴ፤ የእንግሊዙ ክለብ ቼልሲ በሁለት የዝውውር መስኮቶች ላይ እንዳይሳተፍ ያገደው በወጣት ተጫዋቾች የዝውውር ሂደት ላይ ህግ በመጣሱ ነው፡፡
የዝውውር ዕግዱ እስከ ጥር 2020 ድረስ የሚዘልቅ ሲሆን ክለቡ ተጫዋቾችን ለሌላ ክለብ አሳልፎ ከመስጠት፤ በሴት ተጫዋቾች እንዲሁም በፉትሳል ቡድኑ ዝውውር ላይ ከመሳተፍ አያግደውም ተብሏል፡፡
ቼልሲ ከዕግዱ በተጨማሪ የ460 ሺ ፓውንድ ቅጣት የተላፈበት ሲሆን የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበርም ከፊፋ ጋር አብሮ የ390 ሺ ፓውንድ ቅጣት አከናንቦታል፡፡
የፊፋ የስነ ምግባር ኮሚቴ የቅጣት ውሳኔ የተላለፈው ክለቡ ከ18 ዓመት በታች ያሉ የባህር ማዶ ተጫዋቾች ዝውውር ተሳትፎ ላይ ምርመራ ካደረገ በኋላ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ምርመራው ከተመለከታቸው 92 ኬዞች ውስጥ በ29ኙ ላይ ጥሰት መፈፀሙም በፊፋ ተረጋግጧል፡፡
የፕሪምየር ሊጉ ክለብ ግን የቅጣት ውሳኔውን በመቃወም አቤቱታ እንደሚያስገባ አስታውቋል፡፡
ቢቢሲ