loading
አልበሽር ከሚወዷት ስልጣን ተሰናበቱ፡፡

አልበሽር ከሚወዷት ስልጣን ተሰናበቱ፡፡

የዳቦ ዋጋ በዛብን በሚሉ ሰዎች እንደቀልድ የተጀመረው የሱዳን ህዝባዊ አመፅ ከ30 ዓመታት በላይ ሀገሪቱን ለገዙት ኦማር ሀሰን አል በሽር ጦስ ሆኖባዋል፡፡

ለ4 ወራት የዘለቀ አመፅ በማካሄድ አልበሽር ከወንበራቸው ሳይወርዱ ወደ ቤት መግባት የለም ብለው ያለመሰልቸት ጎዳና የከረሙ ሱዳናዊያን ድካማቸው ፍሬ አፍርቷል፡፡

የሱዳን መከላከያ ሀይል በእድሜም በስልጣንም አዛውን ለመባል የበቁትን አልበሽርን ለጊዜው በእስር እንዲቆዩ በማድረግ የ3 ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጓል፡፡

የሀገሪቱ መከላከያ ሚንስትር አብዱልራሂም ሞሀመድ ሁሴን የአልበሽርን መንግስት ተቃውመው አደባባይ በመውጣታቸው በተገደሉ ሰዎች ተቋማቸው ሀዘን የተሰማው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የሱዳን ጦር ሀይል ቀጣዩ ስራው ሀገሪቱን ለ2 ዓመታት የሚመራ ባለ አደራ መንግስት መመስረት እንደሆነም ሚንስትሩ ተናግረዋል፡፡

በቀድሞው ፕሬዝዳንት ሀሰን አልበሽር ለ3 አስርት ዓመታት ስትመራ በኖረችው ሱዳን ከፍርድ ቤቶች በስተቀር ሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች በቀድሞ መዋቅራቸው እንደማይይቀጥሉም ይፋ አድርገዋል፡፡

መከላከያ ሚኒስትሩ አክለውም አዲሱ ባለ አደራ መንግስት ከሁሉም ጎረቤት ሀገራት ጋር የነበረውን መልካም ግንኙነት አጠናሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *