loading
አሜሪካ ከሩሲያ የሚሳኤል መከላከያ ሲስተም ገዝታለች በሚል ምክንያት በቱርክ ላይ ማዕቀብ ጣለች::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 06፣ 2013 አሜሪካ ከሩሲያ የሚሳኤል መከላከያ ሲስተም ገዝታለች በሚል ምክንያት በቱርክ ላይ ማዕቀብ ጣለች:: የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ቱርክ ከሩሲያ የገዛችው የሚሳኤል መከላከያ ስርዓት ለአሜሪካ ደህንነት ስጋት መሆኑን ደጋግመን ነግረናት ነበር ብለዋል፡፡
ዋሽንግተን ያሳለፈችው ውሳኔ የቱርክን ወታራዊ አቅም የማዳከም ሳይሆን የራሷን ደህንነት የማስጠበቅ ነው በማለትም አክለዋል ፖምፒዮ፡፡

ቱርክ ባለፈው ጥቅምት ወር ከሩሲያ የገዛቻቸውን ሚሳኤሎች ለመጀመሪያ ጊዜ መሞከሯ አሜሪካን ይልጥ አስቆጥቷል ተብሏል፡፡ ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው አሜሪካ በቱርክ ላይ የጣለችው ማዕቀብ የመከላከያ ግዥዎችን የሚቆጣጠሩ የመንግስት ኤጄንሲዎች ላይ የኤክስፖርት እገዳና የቪዛ እቀባ ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ቱርክ በበኩሏ በአሜሪካ የተጣለባትን ማዕቀብ ተቀባይነት የሌለውና መሳሪያዎቹ ከኔቶ ሲስተም ጋር የማይጣጣሙ ናቸው የተባለው ምክንያትም ውሃ የማያነሳ ነው ብላለች፡፡

አንዳንድ ተንታኞች እንደሚሉት ትራምፕ ማእቀቡን እስካሁን ያዘገዩት ከኤርዶሃን ጋር ያላቸው ግላዊ ወዳጅነት ነው፡፡ ዋሽንግተን በአንካራ ላይ የጣለችው ማዕቀብ በተዘዋዋሪ ሩሲያ ላይ ያነጣጠረ ስለመሆኑም ከባለስልጣናቱ አፍ ተሰምቷል ነው የተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *