አርጀንቲና ቦነስ አይረስ እየተካደ ባለው 3ኛው የታዳጊዎች ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል እያስመዘገቡ ነው
አርትስ ስፖርት06/02/2011
በትላንትናው ዕለት በ4ኪ.ሜ የአገር አቋራጭ ውድድር ተካፋይ የነበረው የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ማሰልጠኛ ማዕከል አትሌት የሆነው አብርሀም ስሜ ዘጠንኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፤ ከሶስት ቀናት በፊት በተካሄደው የ2000ሜ መሠናክል የትራክ ውድድር ላይ ቀዳሚ በመሆን በማጠናቀቁ እና በሌላ ውድድርም ከርቀቱ የትራክ ተወዳዳሪዎች የተሻለ ሆኖ በማጠናቀቁ በአጠቃላይ ውጤት የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት መሆን ችሏል፡፡
በ800ሜ ለሀገሩ ወርቅ ማስገኘት የቻለው ሌላኛው አትሌት ጣሰው ያዳ፡ ከማጣሪያው ጀምሮ የነበረው አቋም፡ የገባበት ሰአት ፍጥነት እና ሁለቱንም ዙሮች በቀዳሚነት ማጠናቀቅ ችሏል፡፡
በአርጀንቲና እየተከናወነ በሚገኘው 3ኛው የታዳጊዎች ኦሊምፒክ ጨዋታዎች: ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ያስመዘገቧቸው ውጤቶች
1. አብርሀም ስሜ – 2000ሜ መሠ – ወርቅ
2. ጣሰው ያዳ – 800ሜ – ወርቅ
3. መቅደስ አበበ – 2000ሜ መሠ- ብር
4. በሪሁ አረጋዊ – 3000ሜ – ብር
5. አበራሽ ምንስዎ – 3000ሜ – ነሀስ
6. ሒሩት መሸሻ – 800ሜ – ነሀስ
7. መለሰ ንብረት – 1500ሜ – ነሀስ
8. ለምለም ሀይሉ – 1500ሜ – ነሀስ
9.ስንታየሁ ማስሬ – 5000ሜ ርምጃ – በመጀመሪያው ዙር 14ኛ፡ ሁለተኛውን ዙር ደግሞ ዛሬ ምሽት 2:15 ትወዳደራለች::
ውድድሩ መስከረም 26/2011 ዓ/ም የተጀመረ ሲሆን በአጠቃላይ የ13 ቀናት ቆይታ ይኖረዋል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ206 ሀገሮች የተውጣጡ 4000 አትሌቶች በ32 የስፖርት አይነቶች የሚሳተፉ ይሆናል፡
መረጃው፡- ከጋዜጠኛ ኃይለእግዚአብሔር አድሐኖም (ከቦነስ ኤረስ) የተገኘ ነው፡፡