loading
አሸባሪው ህወሓት የእርዳታ መጋዘን በመዝረፉ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል- የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ኮሚቴ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 27፣2013 አሸባሪው ህወሓት የእርዳታ መጋዘን በመዝረፉ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል- የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ኮሚቴ
የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ኮሚቴ አባል የሆኑት ሴናተር ጂም ሪሽ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች የእርዳታ እህል የተከማቸበትን የእህል መጋዘን በመዝረፋቸው ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል አሉ ፡፡ ሴናተሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት አሸባሪው ህወሓት የዩኤስአይዲ (USAID)
መጋዘንን ስለመዝረፋቸው የቀረበው ሪፖርት እንደረበሻቸው ገልጸዋል፡፡ የእርዳታ እህል እንዳይጓጓዝ ያስተጓጎሉ፣ የህይወት አድን ድጋፍን ላልተገባ ዓላማ ያዋሉና እርዳታን እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም በንጹሀን ላይ ግፍ መፈጸም ተገቢ እንዳልሆነ በመጥቀስ እነዚህ አካላት ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤንባሲም ለሴናተሩ ትዊተር ምላሽ ሲሰጥ በአሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል የሚገኙ የዩኤስኤይድ (USAID) መጋዘኖች መዘረፋቸውን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ማግኘቱን ገልጿል። ከኢቲቪ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ህወሓት የድርጅቱን መጋዘን ስለመዝረፉ መናገራቸው የሚታወስ ነው። የአሜሪከ ሴኔት ካለው ቋሚ ኮሚቴዎች መካከል አንዱ የሆነው የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳይ
ግንኙነት ኮሚቴ የአገሪቷን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዎች የሚመራና በሴነቱ ውስጥ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚከራከር፤ አሜሪካ ለአገራት የምትሰጣቸውን ድንበር ተሻጋሪ እርዳታዎችና ድጋፎችን በተመለከተ ሃላፊነት ያለበት ኮሚቴ ነው

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *