አቶ ልደቱ አያሌው ወደ ፖለቲካ ትግሉ ልንመጣ የምንችለው ያፈረሰን የምርጫ ቦርድ እራሱ ከፈረሰ ብቻ ነው አሉ፡፡
ፓርቲ ከሌለኝ በግለሰብ ደረጃ የማደርገው ተሳትፎ ብዙም ጥቅም ይኖረዋል ብዬ አላስብም ብለዋል ለቢቢሲ፡፤
መቀሌ ተዘጋጅቶ በነበረ ጉባኤ መሳተፋቸው ያላስደሰታቸው ወገኖች ዛቻና ማስፈራሪያ እንዳደረሱባቸውና ይህም ለውሳኔ እንዳበቃቸው ተናግረዋል።
ለምን መቀሌ ሄዶ ስብሰባ ተካፈለ ብለው ከፍተኛ የሆነ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍተውብኝ፤ እንገድልሃለን፤ ንብረትሀን እናቃጥላለን የሚሉ መልእክቶች እየደረሱኝ ነው ብለዋል።
በድርጅት ደረጃ የሚያደርጉት አስተዋጽኦ እስከሌለ ድረስ፤ ነጻ ሐሳባቸውን ለመግለጽ በመሞከራቸው ብቻ እንደዚህ ዓይነት ለሕይወት የሚያሰጋ ማስፈራራት የሚደርስባቸው ከሆነ፤ ነገሮች ትንሽ እስኪሰክኑ ድረስ ከየትኛውም ዓይነት የፖለቲካ ተሳትፎ ራሴን መቆጠብ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለው ሲሉ ራሳቸውን ከፖለቲካ ያገለሉበትን ምክንያት አስረድተዋል።
አቶ ልደቱ ከዚህ ቀደም ለአርትስ ቲቪ ኢዴፓ በፍርድ ቤት ከፈረሰ 1 ዓመት ከ8 ወር ሆኖታል ማለታቸዉ ይታወሳል፡፡ያላግባብ ኢዴፓ እንዲፈርስ ተደርጓል ብለዉ የሚያምኑት አቶ ልደቱ ፖርቲያቸውን በማፍረሱ ሂደት የምርጫ ቦርድ ለፍርድ ቤት ምስክር ሆኖ መቅረቡንም ተናግረዉ ነበር፡፡