loading
አዲስ የግብይት አማራጭ ይዞ ብቅ ያለው አሪፍ ፔይ በአሜሪካን ሀገር በሚገኘው የፋይናስ ተቋም አሸናፊሆነ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2013 አዲስ የግብይት አማራጭ ይዞ ብቅ ያለው አሪፍ ፔይ በአሜሪካን ሀገር በሚገኘው የፋይናስ ተቋም አሸናፊሆነ፡፡
አፍሪ ፔይ ሰዎች የዕለት ተዕለት ግብይቶቻቸውን ጨምሮ የመብራትና የውሃ አገልግሎቶችን በቀለሉ መክፈል የሚያስችላቸው የክፍያ ሲስተም ነው፡፡
ይህ ቴክኖሎጂ በተለይም በገጠር አካባቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቀላሉ ግብይት የሚፈፅሙበት እና የብድር አግልግሎት የሚያገኙበት እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡

የአሪፍ ፔይ ፋይናስ ቴክኖሎጂ አክስዮን ማህበር መስራች አቶ ሃብታሙ ታደሰ ቴክኖሎጂው ሰዎች ዕለት በዕለት የሚያደርጉትን የወረቀት ግብይይት በመቀነሰ የክፍያ ስርዓታቸውን እንዲያዘመኑ ከማስቻሉም በላይ በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የባንክ ካርዶችን መቀበል ይችላል ለዋል፡፡ በተለያዩ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች የሚታዩ የኤቴም ካርድ መቀበያ ማሽኖች ችግሮ ያለባቸው ከመሆኑም በላይ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ በመሆናቸው ለከፍተኛ ኪሳራ
ተቋማት ሲዳርግ ይታያል አሪፍ ፔይ ይህንን ያስቀራል ነው ያሉት ሃብታሙ፡፡

አሪፍ ፔይ በቅርቡ አሜሪካን ሀገር በሚገኘው ቪዛ የፋይናስ ተቋም በተደረገው ውድድር ከተመረጡ 100 ሀገራት መሃከል ለመጀመሪያ ግዜ ከኢትዮጵያ ከተወዳደሩ 59 ተቋማት መካከል አሪፍ ፐይ አሸናፊ መሆኑ ታውቋል፡፡ እንደ አቶ ሃብታሙ ገለፃ ከሆነ አሪፍ ፔይ ኢትዮጵያን ከመላው በፋይናንሱ ዘርፍ አለም ጋር ከማስተሳሰር በላይ የሌሎች ሀገራትን ልምድን ለመቅሰም ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል፡፡ በቀጣይም እስከዛሬ ይሰራበት የነበረውን የፋይናንስ አሰራር ለመቀየር ማቀዳቸውን በመግልፅ በተለይ በፋይናንሱ ዘርፉ ኢትዮጵያን ወደተሸለ ደረጃ ለማድረስ ያለመ መሆኑን ነው የተነገሩት፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *