ኢህአዴግ የአርማና ስም ለውጥ አላደርግም አለ
አርትስ 23/01/2011
ሃዋሳ ላይ እየተካሄደ ባለው 11ኛው ጉባዔ ድርጅቱ አዲስ አጀንዳ እንደሌለው ውሎውን በተመለከተ መግለጫ የሰጡት የጉባዔው ቃል አቀባይ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ገልፀዋል።
ድርጅቱ ማምሻውን ከአራቱም ደርጅቶች ፕሬዚዲየም ሰይሞ ሪፖርት መስማቱን የሚቀጥል ሲሆን የአርማና የስም ለውጥ አያደርግም ብለዋል አቶ ፍቃዱ።
ጉባዔው ቀደም ብሎ የገለፀውን መሪ ቃል የቀየረውም ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የሚገልፅ መሆን ስላለበት ነው ብለዋል።