loading
ኢህአዴግ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ሂደት ይቀጥላል አለ

አርትስ 06/03/2011

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ምክር ቤት  አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መግለጫ አውጥቷል፡፡

ምክር ቤቱ በመግለጫው ግንባሩ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ትግል በማስተባበር ለውጦችን ማስመዝገብ የቻለ ቢሆንምሕዝቦችና የተለያዩ የህዝብ አደረጃጀቶችን ለቅሬታና ለምሬት የዳረጉ ጥፋቶች በአመራር ዘመኑ መፈፀማቸውንእንደሚያምን አስታውቋል፡፡

የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በእጅጉ የሚጎዱ አሻጥሮች ሲፈፀሙ፣ የዜጎችና የቡድኖች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችበግላጭ ሲጣሱ እንዲሁም መንግስታዊ ስልጣን ለሽብር ተግባር ማስፈፀሚያ ሲውል ቆይቷል ሲል በመግለጫውተመላክቷል።

በሀገራዊ የፍትህ ስርዓቱ በሀገሪቱ የተንሰራፋውን ሌብነትና ብልሹ አሰራር ትኩረት ማድረጉን ጠቅሷል፡፡ በበዚህምበቅርቡም የተሰጣቸውን መንግስታዊና ህዝባዊ ሃላፊነት ወደጎን በመተውና ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ በአስከፊየምዝበራ፣ የሰብዓዊ ጥሰትና የሽብር ተግባር ስለመሳተፋቸው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ህጋዊ መንገዱን በመከተልበቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከድርጅቱ ህዝባዊ ባህሪ እና አላማዎች ፍፁም በተፃራሪ ድርጊቶች የተሰማሩ ግለሰቦችንና ግብረ አበሮቻቸውን በህግቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር አሁንም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *