ኢራን እስራኤልን ጀብደኝነተሽን አቁሚ ስትል አስጠነቀቀች፡፡
ኢራን እስራኤልን ጀብደኝነተሽን አቁሚ ስትል አስጠነቀቀች፡፡
የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሀመድ ጃቫድ ዛሪፍ እስራኤል የጦርነት ነጋሪት መጎሰሟን ብታቆም ለራሷ ነው የሚበጃት በማለት አስጠንቅቀዋል፡፡
ዛሪፍ ከኤን ቢ ሲ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ሶሪያ ውስጥ የኢራንን ሀይሎች ለማጥቃት የሚደረገው ቅስቀሳ ወደ ከፋ ግጭት ስለሚያመራ ኔታኒያሁ ቢያስቡበት መልካም ነው ብለዋል፡፡
እስራኤል በበኩሏ የኢራን ወታደሮች ከሶሪያ ምድር ጠቅልለው እስካልወጡ ድረስ ድብደባየን አላቆምም ማለቷን ፕሬስ ቴሌቭዥን በዘገባው አስነብቧል፡፡
በ55ኛው የሙኒክ ኮንፈረንስ ላይ ባደረጉት ንግግርም እስራኤል እና አሜሪካ ከኢራን ጋር ጦርነት ውስጥ መግባት ራስን እንደማጥፋት የሚቆጠር መሆኑን ይወቁ በማት አስጠንቅቀዋል፡፡
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያሁ አሜሪካ በኢኮኖሚው እኛ ደግሞ በወታራዊ ሀይል ኢራንን የማዳከሙን ስራ እንገፋበታለን ማለታቸውን ተከትሎ ነው ዛሪፍ ይህን ያሉት፡፡
መንገሻ ዓለሙ