loading
ኢትዮጵያ ቀዳሚ የአለም አቀፍ በረራዎች መሸጋገሪያ ሆነች

አርትስ 20/03/2011

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተከታታይ አምስት ዓመት ከሰሀራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራትና በሌላው የአለም ክፍልበሚደረግ አለም አቀፍ በረራ መተላለፊያ ማዕከል የሚያደርጉ መንገደኞች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ተገልጿል፡፡

ሬውይተርስ በሰራው ዘገባ በ 2018 ደግሞ ኢትዮጵያ ዱባይን በመብለጥ ከሰሀራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራትና ሌሎችየአለም ክፍሎችን በማገናኘት ቀዳሚ መሸጋገሪያ ድልድይ ለመሆን ችላለች ብሏል፡፡

ከ2013 እስከ 2017 ባለው ጊዜ ከሰሀራ በታች በአዲስ አበባ በኩል ወደ አፍሪካ የተደረጉ አለም አቀፍ በረራዎች በ85በመቶ ሲጨምር በዱባይ በኩል የተደረጉ አለም አቀፍ በረራዎች ቁጥር ደግሞ በ31 በመቶ ብቻ ነው የጨመረው ፡፡

በአፍሪካ ነፃ የአየር ቀጠና ባለመኖሩ ከዚህ በፊት በአህጉሪቱና በሌሎች የአለም ክፍሎች የሚደረግ አለም አቀፍ በረራበዱባይ ብቻ ነበር፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *