loading
ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ ግልፅ መርህ አስቀምጣ እየተጓዘች ነው-ኢንጅኔር ስለሺ በቀለ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6፣ 2013 ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ ግልፅ መርህ አስቀምጣ እየተጓዘች ነው-ኢንጅኔር ስለሺ በቀለ

የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ማብራርያ ሰጡ፡፡

ሚኒስትሩ ለዋና ጸሐፊው ግንባታው ስላለበት ሁኔታ፣ ስለሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ስለሚካሄደው ድርድር ተገቢውን ማብራሪያ ሰጥተዋል ።

ኢትዮጵያ በግድቡ ቴክኒካልም ሆነ ህጋዊ መንገዶች ዙርያ ግልፅ መርህ አስቀምጣ እየተጓዘች ስለመሆኑንም አስረድተዋል።

በግድቡ ዙርያ ለሚነሱ ጉዳዮች አፍሪካዊ መፍትሔ የሚለውን መርህ በመከተል አፍሪካ በራሷ ጥበብ ችግሮቿን ሁሉ መሻገር እንደምትችል ለዋና ጸሃፊው አብራርተውላቸዋል፡፡

ይህንም ለዓለም ማሳየት ይቻላል የሚለው ፅኑ እምነት የኢትዮጵያ የማይናወጥ አቋም መሆኑን ኢኒጅኔር ስለሺ በውይይቱ ወቅት መግለጻቸውን ከውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *