ኢትዮጵያ በ7 ወራት ዉስጥ የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት ወደ ዉጭ በመላክ 34 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር አገኘች፡፡
ኢትዮጵያ በ7 ወራት ዉስጥ የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት ወደ ዉጭ በመላክ 34 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር አገኘች፡፡
ወደ ዉጭ ለመላክ ካቀደችዉ 17 ሺህ 386 ቶን የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት ዉስጥ የላከችዉ 11 ሺህ 545 ቶን ነዉ፤ይህም ከእቅዷ 66 በመቶ ብቻ ነዉ ያሳካችዉ ፡፡
በ7 ወር ዉስጥ የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ምርቶችን በመላክ 60.69 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ የተገኘዉ ግን 34.20 ሚሊየን የአሜርካን ዶላር ነዉ፡፡
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በላከልን መግለጫ የወጪ ንግድ አአፈጻጸሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወር ከተላከው ጋር ሲነጻጸር በመጠን እና በገቢ ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ እንደሆነ ገልጿል፡፡