loading
ኢትዮጵያ ቡና የ2011 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ

አርትስ ስፖርት 10/02/2011
ከመስከረም 26 ጀምሮ በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው ውድድር ዛሬ ተጠናቋል፡፡
በመዝጊያ ስነ ስርዓቱ የደረጃ እና ፍፃሜ ግጥሚያዎች ተደርገዋል፡፡
በዚህም ለደረጃ መከላከያ ከ ጅማ አባ ጅፋር ጨዋታቸውን አካሂደው፤ ሙሉ ጨዋታውን 2 ለ 2 በሆነ ውጤት ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ በተሰጠው የመለያ ፍፁም ቅጣት ምት ጅማ አባ ጅፋር 4 ለ 3 በሆነ ውጤት በመርታት ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡
ለዋንጫ ደግሞ ባህር ዳር ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ባካሄዱት ግጥሚያ ደግሞ ቡና 4 ለ1 በሆነ ውጤት በመርታት የዋንጫ ባለቤት ሁኗል፡፡
በጨዋታው ለቡና ድል አቡበከር ናስር ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ሳምሶን ጥላሁንና አል ሀሰን ካሉሻ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ አገናኝተዋል፡፡ ከቡና አራት ጎሎች ሁለቱ በፍፁም ቅጣት ምት የተቆጠሩ ናቸው፡፡ የባህር ዳርን ብቸኛ ግብ ደግሞ እንዳለ ደባልቄ አስቆጥሯል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ይህንን ውድድር ለአራተኛ ጊዜ በማሸነፍ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር እኩል መሆን ችሏል፡፡
በውድድሩ ዳንኤል ደምሴ ከኢትዮጵያ ቡና ኮከብ ተጨዋች የተባለ ሲሆን የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜስ ኮከብ አሰልጣኝ ሁነዋል፡፡ የባህር ዳር ከነማው ግርማ ዲሳሳ መከላከያ ላይ ያስቆጠራት ግብ ምርጥ ጎል ተብላለች፡፡
የስፖርታዊ ጨዋነት አሸናፊ ደግሞ ባህር ዳር ከነማ ሁኗል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *