ኢትዮጵያ የአፍሪካ-ቻይና የንግድ ጉባኤን ልታስተናግድ ነው፡፡
አርትስ 19/03/2011
ኢትዮጵያ የአፍሪካ-ቻይናን የንግድ ትስስርን እንደሚያጠናክር የሚጠበቀውን የአፍሪካ-ቻይና የንግድ ፎረም ከሕዳር 24 እስከ26 ቀን 2011 ዓ.ም በ አዲስ አበባ ልታስተናግድ ነው፡፡
በንግድ ፎረሙ ላይ 41 የቻይና የንግድ ኩባንያዎች ወደ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡
ፎረሙ የቻይና የንግድ ኩባንያዎች በአፍሪካ ካሉ አቻዎቻቸው ጋር የሚኖራቸውን ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር ነው ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፉ ማኅበራት የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዓይናለም ዓባይነህ በሰጡት መግለጫ የንግድ ጉባኤው ለአፍሪካ ሀገራትየተሻለ ትስስር እንደሚፈጥር ገልፀው በዚህ ጉባኤ በ29 ዓይነት የንግድ መስኮች የተሰማሩ የቻይና የንግድ ድርጅቶች ይሳተፋሉ ብለዋል፡፡
በፎረሙ የኢትዮ-ቻይና ኢንዱስተሪያል የትብብር ፎረም መድረክ፣ የኢንቨስትመንት ትውውቅ ጉባኤ፣ በኢትዮጵያ የሚገኙኢንዱስትሪያል ፓርኮች ጉብኝት እና የንግድ ውይይት መድረኮች እንደሚካሄዱም ገልፀዋል፡፡
የቻይና ዓለም አቀፍ የኤግዚቪሽን ማዕከል ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሊ ጃን በበኩላቸው ፎረሙን የቻይና ዓለም አቀፍ የንግድማስታወቂያ ምክር ቤት፣ የቻይና-አፍሪካ የልማት ፈንድ እና ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፉ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር በትብብርየተዘጋጀ መሆኑን ተናግረው ዓላማውም የአፍሪካ-ቻይናን የንግድ ትስስርን ማጠናከር ነው ማለታቸውንሲጂቲኤ ዘግቧል፡፡