loading
ኢንዶኔዢያ 189 ሰዎች አሳፍሮ ጃካርታ ውቂያኖስ ላይ የተከሰከሰዉን አዉሮፕላን ፍለጋ ጠላቂ ዋናተኞችን አሰማርታለች

ኢንዶኔዢያ 189 ሰዎች አሳፍሮ ጃካርታ ውቂያኖስ ላይ የተከሰከሰዉን አዉሮፕላን ፍለጋ ጠላቂ ዋናተኞችን አሰማርታለች

አርትስ 20/02/2011

ሮይተርስ እንደዘገበዉ ዛሬ ጠዋት በጃካርታ ዉቂያኖስ ዉስጥ የአቅጣጫ ጠቋሚ መሳሪያዎችን በመጠቀም የአዉሮፕላኑን ጥቁር ሳጥን ፍለጋ በማካሄድ ላይ የሚገኙት ጠላቂ ዋናተኞቹ በአጭር ጊዜ ዉስጥ እናገኘዋለን ብለዋል፡፡

የኢንዶኔዢያ አቬሽን ገበያ በፈጣን እድገት ላይ ከሚገኙ ሃገራት ተርታ የሚመደብ ሲሆን የአገልግሎት ጥራቱና አስተማማኝነቱ ግን ዥንጉርጉር መልክ ይዟል ተብሏል፡፡ በመሆኑም 189 ሰዎችን ይዞ ከሰማይ ወደ ዉቂያኖስ በሰጠመዉ የአዉሮፕላን አደጋ የተረፈ ሰዉ አለመኖሩም ተነግሯል።

ይህ አደጋ የአለማችን ሁለተኛዉ አሰቃቂ አደጋ ተብሎም ተመዝግቧል፡፡

ከጃካርታ አየር ማረፊያ ረፋድ ላይ ተነስቶ በሰማይ ላይ 13 ደቂቃዎችን ብቻ የተንሳፈፈዉ  ቦይንግ 737 ማክስ 8 አዉሮፕላን ከበረራ ተቆጣጣሪዎች እይታ በመሰወሩ ፓይለቱ እንዲመለሰ ትእዛዝ የተላለፈለት ቢሆንም አዉሮፕላኑ ከዋና ከተማዋ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኝ ዉቂያኖስ ላይ ተከስክሷል፡፡

መንስኤው ባልታወቀው በዚህ አደጋ የተሳፋሪዎቹ አስከሬንም ሆነ የአዉሮፕላኑ አካል  እስካሁን አለመገኘቱን የጠቀሰዉ ዘገባዉ የተሳፋሪዎቹ አልባሳቶች ግን በዉቂያኖሱ ላይ ተንሳፈዉ ተገኝተዋል ብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *