ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ::
ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ::
ኢንጂነር ዘሪሁን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኬሚካል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪ እና በኢንቫይሮመንታል ኢንጂነሪንግ ሁለተኛ ዲግሪ አላቸው፡፡
የስራ ልምዳቸውም በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የከተማና የገጠር ውሃ ፕሮጀክት ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል፡፡ የውሃ ቦርድ ሠብሳቢ እና የምህንድስና ዘርፍ ኃላፊ ሆነው የሰሩ ሲሆን በተጨማሪም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኢንስቲቲውት ኦፍ ቴክኖሎጂ ለሰባት ዓመታት በመምህርነት አገልግለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በድረገጹ እንዳስታወቀዉ ዉሃና መስኖ ኢንጂነሩ በስራ ዘመናቸው ባለስልጣኑ የተቋቋመበትን በቂ ንፁህ ውሃ ለህብረተሰቡ ለማድረስና በከተማዋ የሚፈጠር ፍሳሽ ቆሻሻን በአግባቡ አሰባስቦ ለማስወገድ በተሻለ ትጋት እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡