ኢዴፓ ከሰማያዊ ፓርቲ፣ ከአርበኞች ግንቦት 7 እና ለአንድነትና ለፍትህ ንቅናቄ ጋር ለመወሃድ ውሳኔ አሳለፈ
ኢዴፓ ከሰማያዊ ፓርቲ፣ ከአርበኞች ግንቦት 7 እና ለአንድነትና ለፍትህ ንቅናቄ ጋር ለመወሃድ ውሳኔ አሳለፈ
የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ሁለተኛ ልዩ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል።
ፓርቲው ከጉባኤው በኋላ ከሰማያዊ ፓርቲ፣ ከአርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ለፍትህ ንቅናቄ ፣ ከመኢዴፓና ከሌሎች ፍላጎቱ ካላቸው ፓርቲዎች ጋር ለመዋሃድ ውሳኔ አሳልፏል።
የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ባደረገው ልዩ ስብሰባም የጠቅላላ ጉባኤ አባላቱ በቂ ውይይት በማድረግ ያስቀመጧቸው ተግባራቶች እንዳለቁ ውህደቱን እንዲያስፈጽም የጉባኤውን ሙሉ ውክልና ለስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሃላፊነት መስጠቱ ነው የተነገረው።
ፓርቲው የውህደቱን አስፈላጊነት ጉባኤው ሙሉ ለሙሉ ከስምምነት እንደደረሰበትም በላከው መግለጫ አሳውቋል።