loading
ኢጋድ በቀይ ባህርና በኤደን ባህረ ሰላጤ ጉዳዮች ከሀገራቱ ጋር በቅርበት ይስራል ተብሏል፡፡

ኢጋድ በቀይ ባህርና በኤደን ባህረ ሰላጤ ጉዳዮች በከሀገራቱ ጋር በቅርበት ይስራል ተብሏል፡፡

የኢጋድ አባል ሀገራት አምባሳደሮች በኬንያ መዲና ናይሮቢ ባካሄዱት ስብሰባ የቀይ ባህርና የኤደን ባህረ ሰላጤን በጋራ የሚከታተል ግብረ-ኃይል ለማቋቋም ተስማምተዋል።

የካቲት 20 ቀን 2011 ዓ/ም ጅቢቲ ላይ የተላለፈውን የ46ኛውን የኢጋድ አባል ሀገራት የሚኒስትሮች መደበኛ ጉባኤ ውሣኔን መሠረት አድርጎ ግብረ ኃይሉ የተቋቋመው፡፡

ይህ ግብረ-ኃይል የጉባኤውን ውሣኔዎችና ምክረ-ሀሳቦችን ያጠናል፣ ይከልሳል ያማክራል ነው የተባለው።

በተጨማሪ የበይነ-መንግስቱን አባል ሀገራትን ከቀይ ባህርና ከኤደን ባህረ-ሰላጤ ለሚያጋጥሙ የተለያዩ የጸጥታና የደህንነት ስጋቶች እና  መልካም አጋጣሚዎችን የመለየት፣ የጋራ አቋም የማስያዝና የጋራ አጸፋ የመስጠት ሚና ይኖረዋል ተብሎለታል።

ግብረ-ኃይሉ የሚኒስትሮቹን ጉባኤን ውሣኔዎች ላይ በመመስረት የተሻለ ውጤት ለማምጣት ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ጋርም ተባብሮ ይሰራል  ሲል የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ገልጿል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *