loading
ኤርዶሀን በኢምፔሪያሊስት ዓለም መኖር አንፈልግም አሉ

ኤርዶሀን በኢምፔሪያሊስት ዓለም መኖር አንፈልግም አሉ

አርትስ 28/02/2011

 

ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሀን  ይህን ያሉት አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለቸውን ከምንጊዜውም የከፋ የተባለውን አዲሱን ማእቀብ በመቃወም ነው፡፡

አናዶሉ የዜና ወኪል እንደዘገበው ፕሬዝዳንቱ ሀገራቸው በአሜሪካ ህግ እንደማትገዛና በኢራን ላይ የጣለቸውን ማእቀብ አጥብቃ እንደምትቃወም ተናግረዋል፡፡

ዋሽንግተን በቴህራን ላይ የጣለቸው ማእቀብ ዓለም አቀፉን ህግ የሚፃረር ነው ያሉት ኤርዶሀን አሜሪካኖች ዓለም ሚዛ ኗን ጠብቃ እንዳትቀጥል ተግተው ይሰራሉ በማለት መረር ያለ ትችታቸውን ሰንዝረዋል፡፡

በአዲሱ ማእቀብ መሰረት ከኢራን ነዳጅ እንዲያስገቡ ከተፈቀደላቸው ስምንት ሀገራት መካከል የቱርክ ስም ቢካተትም ፕሬዝዳንቱ አሜሪካን ከመውቀስ አልተቆጠቡም ይላል ዘገባው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *