እስራኤል በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2020 በጋዛ ሰርጥ 300 ጥቃቶችን መፈፀሟን ይፋአደረገች::
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣ 2013 እስራኤል በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2020 በጋዛ ሰርጥ 300 ጥቃቶችን መፈፀሟን ይፋአደረገች:: የሀገሪቱ መከላከለያ ተቋም ባወጣው መግለጫ በአካባቢው በተመረጡ 300 ኢላማዎችላይ ጥቃት ማድረሱንና 38 የጥቃት ሙከራዎችን ማክሸፉን ተናግሯል፡: ከጋዛ በኩል 176 ሮኬቶች ተተኩሰውብን ነበር ያለው የእስራኤል ጦር ሃይል ከነዚህ ውስጥ 90 በመቶ የሚሆኑት ባዶ ሜዳ ላይ ነው ያረፉት ብሏል፡፡
በሪፖርቱ እንደተገለፀው የእስራኤል ተዋጊ አውሮፕላኖች በርካታ የቅኝትና የማጥቃት ግዳጆችን ሲፈፀሙ ሰው አልባ የስለላ አውሮፕላኖች ደግሞ በአካባቢው ለ35 ሺህ ሰዓታት ያህል መብረራቸው ተሰምቷል፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ካለፈው 2019 ይልቅ በ2020 በርካታ ጥቃቶችን አድርሳለች፡፡ የተባበሩት መንገስታት ድርት በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት እስራኤል በ2020 በጣም ከተወገዙ ሀገራት ተርታ ግንባር ቀደም መሆኗን አስታውሷል፡፡
ድጅቱ በሪፖርቱ እንዳለው ከእስራኤል ቀጥለው በብዙ የተወገዙ ሀገራት ሰሜን ኮሪያ፣ ኢራን፣ ሶሪያ ማይናማርና ክሬሚያ ናቸው፡፡ የመንግስታቱ ድርጅት እስራኤልን የሚያወግዙ 17 ውሳኔዎችን ያወጣ ሲሆን ይህም ከቀሪው ዓለም ጋር ሲፃፀር በሶስት እጥፍ ይበልጣል ነው የተባለው፡፡