እንግሊዝ ከኢትዮጵያ ከወሰደቻቸው ቅርሶች ውስጥ 11 ፅላቶች በእንግሊዝ መኖራቸው ተገለፀ
እንግሊዝ ከኢትዮጵያ ከወሰደቻቸው ቅርሶች ውስጥ 11 ፅላቶች በእንግሊዝ መኖራቸው ተገለፀ
በመቅደላ ጦርነት ወቅት እንግሊዝ ከኢትዮጵያ ከወሰደቻቸው ቅርሶች ውስጥ በቅርቡ ወደሀገሩ የተመለሰው የንጉስ አፄ ቴዎድሮስ ሹሩባን ጨምሮ 11 ፅላቶቸ መኖራቸውን የበህል እና ቱሪዝም ሚንስቴር ሚንስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ተናግረዋል፡፡
በታሪክ አጋጣሚ ከሀገር ተወሰደው ከቀሩ የኢትዮጵያ ቅርሶች መሀከል ከ 349 በላይ የብራና መፅሃፍት መኖራቸውንም የጠቀሱት ሚኒስትሯ እነዚህ ቅርሶች ለሀገራችን ህዝብ የሚሰጡት ፋይዳ በምንም የማይታካ በመሆኑ ከእንግሊዝ ሀገር ጋር በተደረገ ደርድር በቅረቡ ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ተናግረዋል፡፡
እንግሊዞች ለ151 ዓመት ያህል ጠብቀው ያቆዩትን ቅርሶች አሁን ያለው ትውልድ ተረክቦ ቅርሶቹን በሚገባ የመንከባከብ ሃላፊነት እንዳለበት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳው ተናግረዋል፡፡