loading
ኦብነግ በሶማሌ ክልል ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ከመንግስት ጋር ተስማምተናል አለ

አርትስ 14/02/2011

 የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ኦብነግ የሶማሌ ህዝብ ከኢትዮጵያ መገንጠልም  ሆነ መቆየት ከፈለገ  መብቱ እንዲከበር  ህዝበ- ውሳኔ ለማድረግ ከመንግስት ጋ መስማማቱን አስታወቀ።

የግንባሩ የውጭ ግንኙነት ፀሐፊ አቶ አህመድ ያሲን ሼክ የሶማሌ ህዝብ ዕጣ ፈንታውን በነፃነት መወሰን እንዳለበት ከኢትዮጲያ መንግስት ጋር ስምምነት  መድረሱን  ተናግረዋል።

ግንባሩም የሚታገልለትን አላማም በሰላም እንዲያስቀጥል እንዲሁም  የህዝቡ  ውሳኔ እንዲከበር ተስማምተናል  ብለዋል። ህዝበ ውሳኔውንም ለማስፈፀምም ከኢትዮጵያመንግሥት ጋር የሁለትዮሽ ኮሚቴ እንደሚመሰረትም ተናግረዋል።

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር(ኦብነግ) በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን የመንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት  መግለፃቸው ይታወሳል ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *